አዳም ረታ፡ ጥልቀት ያለው የኢትዮጵያ ድምፅ! ቃሎቹ ልብን ይማርካሉ፣ ስሜትን ይነካሉ፣ ጥልቅ ሀሳብም ያጭራሉ።
“አዳምን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል።”
— በእውቀቱ ስዩምአዳም ረታ ከ 1970ዎቹ ጀምሮ አጫጭር ልብ ወለዶችን፣ ግጥሞችና የረዥም ልብ ወለድ ድርሰቶች መፃፍ ጀምሯል። “ማሕሌት” በ 1981 ከታተመ ወዲህ ለኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ቀዳሚ ድምጽ ሆኗል።
ሥነ-ጽሑፋዊ ፍልስፍናው ከአገራችን አንኳር ቁሳቁስ ይፈልቃል — ከእንጀራ፣ ከጉርሻ፣ ከልቃቂት፣ ከአደይ አበባ — አገሬው የሚኖረውን ዕለታዊ ሕይወት ቀምሮ በሥነ-ጽሑፍ አቅርቦታል።
ተጨማሪ ያንብቡ →ከዘመናዊ አጭር ልብ ወለድ… የአዳም ረታን ማሕሌት እወዳለሁ። የኢትዮጵያውያንን ልብ አውቄበታለሁ።
[አዳም] ከአገረሰባዊ እሴቶች — ከእንጀራ፣ ከጉርሻ ቅርፅ ወስዶ ተናጥላዊ ኢትዮጵያዊ ንፅረተ ዓለምን ለመቅረፅ ደፍሯል።
እንደ ተወርዋሪ ኮከብ የብርሀን ፈለጉን ከኋላው እየተወ በትውልዶች ሕዋ ላይ ለረጅም ዘመን የሚታይ ደራሲ አዳም ረታ ብቻ ነው።
አዳምን ያላየ ምንጭ ያመሰግናል።
ሁሉም ዜናዎች፣ ሒሳዊ ትንተናዎች፣ ቃለ-መጠይቆች ወዲያው ይደርሱዎታል